Interview avec les azmari Aklilu Ǧämäru (masinqo et voix) et Haylé Gäbrä Mika'él (voix), à Aliyu Amba, le 23 mai 1996, réalisé par Anne Bolay et Ambaye Yilma. ድማማ፡ድማማ፡ ድማማ፡ድማማ፡ ረ፡እንደምን፡አለህ፡ስስቴ፡እራቁቴ፡ በቆላም፡በደጋም፡ስስቴ፡እራቁቴ፡ ስስቴ፡እራቁቴ፡የነእሸቴ፡ወንድም፡ ስስቴ፡እራቁቴ፡የዘገዬ፡ወንድም፡ ደሞ፡የሴቶቹ፡ደሞ፡የወንዶቹ፡ የደምሴ፡ወንድም፡ስስቴ፡እራቁቴ፡ ይሄ፡ሞት፡አለና፡??? ገላ፡ገላ፡ገላ፡ እንዲያው፡ገላ፡ገላ፡??? ለጨዋታው፡ለመነጋገሩ፡ ጥቁር፡ነው፡ይላል፡ጥቁር፡ያርጋቸው፡ እኔ፡እንደምወድህ፡ማን፡በነገራቸው፡ ረ፡እንደምን፡አለህ፡ እስቲ፡በገበየሁ፡በግዛቸው፡ሞት፡ እስቲ፡በደምሴ፡በዛ፡በሰው፡ሞት፡ ?? የግዛቸው፡ወንድም፡ አንተን፡አይደለም፡ወይ፡ እኔ፡እማጫውተው፡ አነሰ፡ቀጠነ፡ብሎ፡ይማይለኝ፡ሰው፡ እንግዲህ፡ጀመረ፡አንገቱን፡ያሽዋል፡ የበላው፡ይመስል፡አሪዙን፡ያሽዋል፡ የበላው፡ይመስል፡አሪዙን፡ያሽዋል፡ ገበሬ፡ነህ፡አሉኝ፡ጥጥር፡መሬት፡አላሽ፡ እኔም፡ትንሽ፡አለኝ፡ለበሬ፡ተመባሽ፡ እንከትክት፡አልኩኝ፡ተሰበሬ፡ጐኔ፡ አወይ፡አወደደቅ፡መኝታ፡አላውቅ፡እኔ፡ ግዛቸው፡ወፈረ(አረጀ)፡ቀንዱ፡ከለከለው፡ ደሞ፡በሚጠጣው፡ተኮለኮለ፡