Enregistrement réalisé à Wäldiya avec la chanteuse Gurädo Habtu et l’azmari Tägäññ Däbay, le 25 avril 2000, par Anne Bolay et Ambaye Yilma. anči hoyé ኧኸከ፡ኸ፡ነ፡ኔ፡ እንዴት፡አደራችሁ፡ሰው፡እንደ፡ፀባዩ፡ ዳመና፡እሞቃለሁ፡እስኪወጣ፡ፀሐዩ። እዬ፡ያገሬ፡ልጅ፡ነ፡ በድላኝ፡በድላኝ፡በደሏ፡ልክ፡የለው፡ ሄድኩኝ፡ተመልሼ፡ለልቤ፡ልብ፡የለው። ኸ፡ነ፡ነ፡ ኸ፡ነ፡ነ፡ የከሌ፡እከሌ፡አለው፡ማለቱ፡ደግ፡ነው፡ እዳውን፡ጨራሹ፡ያው፡ባለ፡ቤቱ፡ነው። እራያና፡ቆቦ፡ሰፊ፡አገር፡እያለ፡ እዚህ፡ከጠባቡ፡ከሆዴ፡ሰው፡አለ። ከሆደ፡ሰው፡አለ፡ሌሌ፡ መልካም፡የወለደ፡ይጠራል፡በልጁ፡ ሸጋ፡የወለደ፡ይጠራል፡በልጁ፡ ጀግና፡የወለደ፡ይጠራል፡በልጁ፡ የጎበዞች፡አገር፡እንደምነሽ፡የጁ። የበርበሬው፡አገር፡አላገዶ፡ነው፡ ቅመሙን፡ሙጋድ፡ላይ፡ምን፡አበቀለው። አሻግረን፡ብናየው፡ቃለም፡መለስ፡ለሱ፡ የባላባቱ፡አገር፡የባለ፡ቀሚሱ። እኸ፡ኔ፡ኔ፡ኔ፡ እናትና፡አባትሽ፡አይወዱም፡እንግዳ፡ ሳሚኝ፡እና፡ልሂድ፡በሳቃው፡ቀዳዳ። እመጣለሁ፡ብሎ፡ሰው፡እንዴት፡ይዋሻል፡ ማበል፡እንኳን፡አንቺን፡ምድር፡ያበላሻል፡ ምድር፡ያበላሻል፡ሌ፡ሌ ሴትን፡አትመኑ፡ሞላ፡ትበላለች፡ እኔን፡ትላንት፡ማታ፡ሙት፡ብላኝ፡ቀርታለች፡ እነ፡ኔ፡ነ፡ነ፡ እየው፡ያገሬ፡ልጅ፡እየው፡ያገሬ፡ልጅ