Entretien réalisé par Anne Bolay et Ambaye Yilma à Amanuél (Goǧǧam) avec l’azmari Käbrit Asäffa, le 8 juin 1998. L’original a été enregistré sur la cassette DAT K/98. ምነው፡ምነው፡ ምነው፡ላሞቻችን፡ከድንበር፡የዋሉ፡ ያሣር፡አይደለምወይ፡የምናየው፡ሁሉ። ወይስ፡አልታጨዳ፡ወይ፡ከብት፡አልበላው፡ ከቶስ፡መቼ፡ይሁን፡የአለም፡ያሳር፡ማለቂያው። ጠሉኝ፡ዘመዶቼ፡እኔ፡ስወዳቸው፡ ያጣ፡ሰው፡አያገኝ፡እየመሠላቸው። ያገኘም፡ያጣና፡ያጣም፡ያገኝና፡ ያስተዛዝበናል፡ያቀን፡ይመጣና። እኔ፡ገዳዬ፡ እኔ፡ምንቸገረኝ፡ያወራ፡ቢያወራ፡ እስቲ፡አንቺን፡ያሰንብት፡ከጓደኛሽ፡ጋራ፡ እስቲ፡አንቺን፡ያሰንብት፡ከጓደኛሽ፡ጋራ። የተመረቀች፡ናት፡አባት፡መርቋት፡ ትምርቱን፡በመሉ፡ለሷ፡የሠጣት። ቀይ፡አልነበርሽም፡ወይምን፡አጠቆረሽ፡ ባልታጠበ፡እጃቸው፡እየነካኩሽ። ተምሮ፡ተምሮ፡ቦታ፡ካልሰጡት፡ በጣም፡ያሳዝናል፡ሲባክን፡እውቀት። ገዳዬ፡ገዳዬ፡ገዳዬ፡ገዳዬ ከጠራው፡ሜዳ፡ላይ፡ምንድነው፡ወለሌ፡ የናጅሬ፡እህት፡ገዳዬ፡ገዳዬ፡ መጣለች፡ምስጥሬ፡ ሆ፡ጌዳሙ፡ገዳዬ፡ገዳዬ፡ ራሱን፡ገዳለው፡ቼ፡ብሎ፡ቼ፡ብሎ፡ ከመቀካር፡በላይ፡ስም፡ይቀራል፡ብሎ። ደህና፡ጎበዝ፡ሲሞት፡ሳቀ፡ጅሩ፡ጅሩ፡ጅሩ፡ሰው፡ የታገተ፡ጥጃ፡የማያስመልሰው። ደህና፡ጎበዝ፡ሲሞት፡ደስ፡ይለዋል፡ጅል፡ አገሩ፡ሲወረዳ፡የማይደፈር።