Chant enregistré à Mäkänä Sälam auprès e la chanteuse Yarom Gärämäw et du joueur de masinqo Asäga Husen Mängäša par Anne Bolay et Ambaye Yilma, le 24 novembre 1999. tezeta ኸ፡ድማሜ፡ነሽ፡ ተመስገን፡ልበል፡ አምላክ፡አልማ፡አሉ፡ እንኳን፡ለዘንድሮ፡ለዚያ፡ሰሞን፡ ኸ፡ኸ፡ እናቴን፡ተይ፡በሏት፡ እናቴን፡ተይ፡በሏት፡ እርግማኗን፡ትተው። ትዘንልኝ፡ለኔ፡ለምከራተተው። ወይንም፡ያሳብ፡አይሉሽ፡ወይንም፡የትዝታ፡ ሰው፡አባክኖ፡ገዳይ፡እዴነሽ፡ትዝታ፡ ነ፡ነ፡ኸረ፡ነ፡ነ፡ ወትሮ፡አባቶቻችን፡ተኳሾች፡ነበሩ፡ ወትሮ፡አባቶቻችን፡ተጨዋች፡ነበሩ፡ እኛን፡ያፈዘዘን፡ምንድነው፡ነገሩ፡ ሽቅለን፡ሸቃቅለን፡እንግባ፡አገራችን። እንዳወጡ፡ቀሩ፡አይበል፡ጠላታችን፡ የኔ፡አለም፡ቢሻኝ፡ጐጃም፡ነው። የኔ፡አባት፡ትልቅ፡ነው፡ የኔ፡አባት፡ትንሽ፡ነው። ትንሹም፡ትልቅ፡ነው፡እጀራ፡ሲያገኝ። የአምባሰል፡ማር፡ቆራጭ፡የወርዳል፡በገመድ፡ አደራ፡ቢሰጡት፡ይባላል፡ወይ፡ዘመድ፡ እኝህ፡አባሰሎች፡አበላል፡ያውቃሉ፡ በገብስ፡እንጅራ፡ላይ፡ሳም፡አርጉ፡ይላሉ። አምባሰል፡ለገደል፡መች፡ያሽሟጡጡታል፡ ፈረስ፡ባያስጋልብ፡ማር፡ይቆርጡበታል፡ ማር፡ባይቆረጠው፡ልጅ፡ይወጣበታል። አረግ፡እንደምነሽ፡አረግ፡እንደምነሽ። አንቺ፡ስትተይው፡እኔ፡አልተወውም፡ወይ። የዛፍ፡ጥላ፡እንኳ፡ይዟዟር፡የለም፡ወይ። ቤትሽና፡ቤቴ፡አግድመት፡ላግድመት፡ አንገቴ፡ጠነነ፡ስጋ፡እዳየ፡ድመት። ኧረ፡ሶዬ፡ሶዬ፡ከተማው፡ መቢያ፡ቢጠፋ፡ይበላል፡እንደያው። እተወለድኩበት፡አብ፡የለም፡አገሬ፡ አላደኩበትም፡እዲያው፡ደስ፡ይለኛል፡ እደያው፡ደስ፡ይለኛል፡መቀሌ፡ቢሉት።