Chant enregistré dans un bar à Qay Mäbrat auprès d’un joueur de masinqo et chanteur non identifié par Anne Bolay et Ambaye Yilma, le 29 novembre 1999. ambasäl እንዴት፡ነሽ፡እንዴት፡ነሽ፡ እንደያው፡መላ፡መላ፡ ኧረ፡መላ፡መላ፡ አንድ፡አይኔን፡አሞቷል፡ እልም፡ድርግም፡ይበል፡ እኔ፡እና፡እንቺ፡ደህና፡ብዙ፡አይተንበታል፡ የስጋ፡እሸት፡አለ፡ጨጓራ፡እና፡ጉበት፡ እስኪ፡ሰው፡ፈልጉ፡ታማኝ፡እሚላክለት፡ በልጅጌን፡አቁሜ፡ወንድሞቼን፡ትቼ፡ እንዲያው፡ምን፡አደረኩ፡በሰው፡ተመክቼ፡ ከቀይ፡መብራት፡ወዲያ፡በሩን፡አገሬ፡ነው፡ ፍቅር፡ይደረሳል፡ትዳር፡በኃላ፡ነው። ታይሆነኝ፡አግብቼ፡ታይሆነኝ፡ወልጄ፡ ልቤ፡ወደ፡ሴቷ፡አይኔ፡ወደ፡ልጄ፡ እንዴት፡ነሽ፡ ባማች፡ይበቀላል፡የዘመኑ፡ሰው፡ አይቶ፡መጋባት፡ነው፡ከሚጠቅም፡ሰው፡ ከኮበልሻ፡በታች፡ከደሴ፡በታች፡ ሐረጎ፡ጥጉ፡ላይ፡ያገኘናት፡ልጅ፡ በእጅ፡አትኩኝ፡አለች፡በከንፈር፡ብቻ፡እንጂ፡ እዴነሽ፡እንዴነሽ፡ድማሙ፡ድማሙ። እዴነሽ፡እንዴነሽ፡ኧረ፡መላ፡መላ፡ ወንድም፡እንዴት፡ይሙት፡ ዘመድ፡እንዴት፡ይሙት፡ የቸገረው፡ለታ፡ውለታ፡እሚሆን። እህት፡እንዴት፡ትሙት፡ የራከሙ፡ለታ፡የምትሆነውን፡ ባዳ፡ይሙት፡እንጂ፡እሚከዳውን። ሴትን፡አትመኑ፡ውላ፡ትከዳለች፡ እኔን፡አሁን፡ለታ፡ሙት፡ብላ፡ቀርታለች።