Chant enregistré à Mäkänä Sälam auprès e la chanteuse Yarom Gärämäw et du joueur de masinqo Asäga Husen Mängäša par Anne Bolay et Ambaye Yilma, le 24 novembre 1999. አድነን፡እግዚዮ፡ አትጥራን፡በከንቱ፡ ገና፡በፉካሬ፡መሽች፡ ጀንበሪቱ፡ አምላኬ፡አምላኬ፡ምን፡አልኩሀ፡ ጠጅ፡አስለምደህ፡ደሞ፡ውኃ። አባቶቻችን፡በቅሎ፡ገዝተው፡ ኮርቻ፡ነበር፡አሳባቸው፡ የዛሬ፡ልጆች፡እጅግ፡ኮሩ፡ ለመርገፍ፡ነው፡የሚጥሩ። ኽ፡ኸ፡ኸ፡ ማን፡እናት፡አባቱን፡ይዞ፡ይሰደዳል፡ ማን፡አክስት፡አጎቱን፡ይዞ፡ይሰደዳል፡ ባህሪን፡ካሳመሩ፡ባዳም፡ሰው፡ይወዳል። ፀባይ፡ካሳመሩ፡ባዳም፡ሰው፡ይወዳል። አሁን፡በሜንታ፡ላይ፡የነበረ፡በሬ፡የነበረ፡ኮርማ፡ አሁን፡በጫቃታ፡የነበረ፡ላም፡ አሁን፡በራቻ፡ላይ፡የነበረ፡ላም፡ ወድቆ፡ወድቆ፡አለቀ፡ያ፡ሁሉ፡ቀንዳም። ቅዱሱን፡አዳም፡ሲፈጥረው፡ አላንድ፡ዘመድ፡አላንድ፡ሰው፡ አብራሃም፡ልጁን፡መረቀው፡ ና፡ተባረክ፡አለው። ከጎጃምና፡ከዳሞት፡ማን፡ይበልጣል፡በስፋት፡ እኛም፡ብናየው፡ብንተቸው፡ትልቁ፡ደሞት፡ነው። አንተማ፡ወዳጄ፡አንተማ፡ዘመዴ፡ አንተማ፡ያገር፡ልጅ፡አልነበርክም፡ወይ፡ ገደልከኝ፡ቀበርቀኝ፡ካልሰማ፡ሳላይ። እኔ፡አንተ፡ብዬ፡ብከተል፡አይቼ፡ ሞትምን፡ያህል፡አደጋ፡አንተን፡አስቀምጨ። በፈረስ፡በበቅሎ፡ወረድኩኝ፡ምነው፡ ያባት፡ምስክሩ፡ልጅ፡ሲወጣ፡እኮነው፡ ካላባት፡ካለእናት፡አይፈጠርም፡ሰው፡ ብቻውን፡ይቀራል፡ሞት፡ይተጨረሰው። ትንንሽ፡አገልግል፡ሰፍተሽ፡ አታንገላቻት፡እባክሽ፡ ያሞት፡በመጣ፡ምነው፡ ገላ፡አፈር፡እኮነው።