Chant enregistré à Ilada auprès du joueur de masinqo et chanteur Ṣägaw Käbädä par Anne Bolay et Ambaye Yilma, le 1er décembre 1999. sälämon ኧረ፡እንደምን፡አለሽ፡ እየተወያየን፡ተምሮ፡ስፍራ፡ካልሰጡት፡ አያል፡ያሳዝናል፡ሲባከን፡እውቀት፡ እናት፡አወድማናት፡የተለቀለቀ፡ ቢበሉት፡ቢጠጡት፡አትልም፡አለቀ፡ ኧረ፡ግዳዬ፡ገዳዬ፡ነይ፡ ኧረ፡ነይ፡ ኧረ፡ነይ፡ ትምህርት፡የተማረ፡መውደቁን፡አናውቅም፡ እራሱን፡ይችለል፡ባባቱም፡ባይጠቅም፡ ኧረ፡ ኧረ፡ ለሰሱም፡ተምሮ፡ሰውም፡አህምሮ፡ነው፡ የጉበላዬው፡የተገናኘ፡ነው። የመጣችሁትም፡ወደላይ፡ወደላይ፡ ለኛ፡ማደጊያ፡ነው። አምላክ፡አይለየን፡ጨዋታ፡ደግ፡ነው፡ እታች፡ዱቄት፡ወሶዶ፡አይበላም፡አንጉቶ፡ እዮት፡ተመልከቱት፡መቷል፡ለኛ፡አንባቶ፡ ኧረ፡ነይ፡ አባት፡የሌለው፡ልጅ፡ አናት፡የሌለው፡ልጅ፡ አይበላም፡ትኩስ፡ እሞሶብ፡ቁጭ፡ብሎ፡ካልመታው፡ንፈስ፡ ደሞ፡ነይ፡ደሞ፡ነይ፡ እርጥቡን፡ደረቁን፡ትበላለች፡ላም፡ አወይ፡ደብረ፡ሲና፡መካነ፡ሰላም፡ ገንዘብ፡ያልቀል፡እንጂ፡ጓድ፡አይከዳም፡ እኔስ፡ጓደኛዬን፡መክዳቴ፡ለምነው፡ ገንዘብ፡የተሰራው፡ከሠው፡በኃላ፡ነው።